ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በ 2012 የድህረ ምረቃ በመደበኛ እና በርቀት ትምህርት ለመጀመር የሰራ ነው

ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በ 2012 የድህረ ምረቃ በመደበኛ እና በርቀት ትምህርት ለመጀመር የሰራ ነው

ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በኢትዮጲያ የጥራት ደረጃ ኤጀንሲ የተዘጋጁት ስታንዳርዶች በተገቢው መልክ በመፈፀም በ2012 ዓ/ም በተቋም ደረጃ አይ ኤስ ኦ (ISO) ሰርቲፊኬት ለማግኘት የሚያስችለውን ተግባራት  እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው የትምህርት አሰጣጥ ጥራት ደረጃውን በማሳደግ አዳዲስ የድህረ ምረቃ በመደበኛ እና በርቀት ትምህርት ለመጀመር ለዚሁ ተገቢ የሆነ እውቅና ለማግኘት የሚያስችለው ብቃት ላይ ይገኛል።

በቴክኒክና ሙያ ኮሌጀች የትምህርት ሥልጠና ጥራት ለማስጠበቅና   በየሙያ ደረጃው የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ አድርጓል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ  የማስልጠኛ መሳሪያዎች (TTLM) ዝግጅት በሁሉም የብቃት አሃዶች ማዘጋጀቱንና የትብብር ሥልጠናን አፈፃፃምን የሚያሻሻሉ  የተለያዩ ተገባራት እያከናወነ መሆኑን ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋክል።      

አቶ ብርኑ አያይዘውም  የምዘና ሥርዓቱን  ለማጠናከርና በዩኒቨርስቲው የሚተገበረውን የተከታታይ   ማጠቃለያና ተቋማዊ ምዘና   ዝግጅትና አፈፃፃም ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን መደረጉንም አስረድተዋል።

በኢትዩጵያ የደረጃ ኤጀንሲ (Ethiopia Standard Agency )የተዘጋጅ   ስተንደርዶችን ማለትም  የስርዓተ ትምህርት (Curriculum Requirement  ES. 6259-1 : 2018) ፣

የመሳሪያዎች ማሽነሪዎች( Tools machines & Equipment requirement ES 6259-8 : 2018)፣  የምዘናና የማሰልጠኛ መሳሪያዎች (Assessment & Instructional Materials ES 6299-9: 2011 ) እና የመሳሰሉትን   ተግባራዊ እያደረገ ፡መሆኑን አቶ ጸጋይ  ገልጸዋል፡ ምክትል  ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም በዩኒቨርሲቲው የሚስጠውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በምርምር ለማገዝ እንዲቻል የተለያዩ  ጥናቶች በማካሄድ  ያሉ ችግሮችን የመለየት ስራ በየጊዜው እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Pin It on Pinterest