ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአገር ውስጥ እና በውጪ አገራት ( በሱማሌ ላንድ እና ፑንት ላንድ ) በሚገኙ ካምፓሶቹ በዲግሪ እና በቴክኒክ ሙያ ትምህርት እና ስልጠና መርሃ ግብሮች 3ሺ 200 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተማሪዎቹ በአካውንቲንግ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ ሶሾሎጂ ፣ ነርሲንግ እና በሌሎች ትምህርቶች የተመረቁ ናቸው።

በኦሮምያ ባህል  አዳራሽ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ማቲዎስ ጊቺሌ የተማሪዎቹን መመረቅ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርስቲው ላለፉት 18 ዓመታት በአገሪቷ የልማት እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን የተማረ የሰው ሃይል በማሰልጠን ረገድ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል:በተጨማሪም ክ ሀገር ግንባታ ኣልፎ ክ 22 የተለያዩ የአፍሪካ ዜግጎች በተለያዩ ዘርፎች በማስልጠን የበኩሉን ድርሻ የተወጣ ይገኛል።

«ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ጥራቱን ከምንግዜውም በላይ ለመጨመር፤ በጥናት እና ምርምር ላይ አስተዋዕፆ ለማበርከት እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ያለውን ብርቱ እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላል» ያሉት ፕሬዚዳንቱ የዘንድሮው ተመራቂዎች፤ ተመራቂዎች በአገሪቱ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ እራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና አገራቸውን ለማገልገል በታማኝነት መሳተፍ እንዳለባቸው ገለጹ በተመረቁበት የሙያ ዘርፍ አገራቸውን በጥሩ ስነ ስነምግባር ማገልገል እንዲችሉ አሳስበዋል።

ዩኒቨርስቲው ባለፉት 18 ዓመታት በመደበኛ ፤ በዲግሪ፣ በዲፕሎማ በሰርተፍኬት ከ60 ሺ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል። በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት በዲግሪ እና በቴክኒክ ሙያ በመደበኛው ትምህርት በአገር ውስጥ እና በውጪ አገራት ( በሱማሌ ላንድ እና ፑንት ላንድ ) ከ10 ሺ በላይ ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል።

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

NGUC Social apps share this post with your friends!

Shares